Friday, 4 April 2014

 
ገዥው ፓርቲ ሲኣን/መድረክ በሃዋሳ ከተማ የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ ለማደናቀፍ ያደረው ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ ተሰማ
April 04, 2014
ሲኣን/መድረክ ባለፈው ሳምንት በሃዋሳ ከተማ የፖለቲካ ፕሮግራሙን ለኣባላቱ እና ለደጋፊዎቹ ለማስተዋወቅ የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ ገዥው ፓርቲ የመሰብሰቢያ ኣዳራሽ በመከልከል እና የሲኣን/መድረክ ኣባላት በስብሰባው ላይ እንዳይሳተፉ ተጽዕኖ በማድረግ ለማድናቀፍ ያደረጋው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
 
ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ እንደዘጋበው የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ከመድረክ ጋር በመተባበር በሃዋሳ ከተማ ባለፈው ሳምንት ያከሄደው ታላቅ ህዝባዊ ጉባኤ ልካሄድ የነበረው መጋቢት 2/2007 /ም ቢሆንም፤ የሲዳማ ዞን እና የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ኣዳራሽ በመከልከላቸው የተነሳ ወደ መጋቢት 20 2006 /ም ለማስተላለፍ መገደዱ ታውቋል።
 
ጉባኤውን ለማካሄድ እንደኣማራጭ ተይዞ ከነበሩት መሰብሰቢያ ኣዳራሾች መካከል የሲዳማ ባህል ኣዳራሽ ኣንዱ ሲሆን፤ ባህል ኣዳራሹን የሚያስተዳድረው የሲዳማ ዞን ኣዳራሹ በተመሳሳይ ቀን በሌላ ሰብሰባ መያዙን የምገልጽ ምላሽ ሰጥቷል።
 
በሁለተኛ ኣማራጭነት የተያዘው በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ የምገኙ ኣደራሾች ሲሆን፤ የከተማዋ ኣስተዳደር የመሰብሰቢያ ኣዳራሽ እንድፈቅድ በደብዳቤ ተጠይቆ ዛሬ ነገ በማለት ምላሽ ሳይሰጥ ቆይቶ በኃላ ላይ ኣዳራሽ እንደሌለው በመግለጽ ምላሽ መስጠቱ ታውቋል።
 በህዝብ ገንዘብ ለህዝብ ግልጋሎት እንድሰጥጡ የተገነቡትን እንዚህ ኣዳራሽ ለመጠቀም የተደረገው ጥረት በገዥው ፓርቲ ኣስተዳደሮች በመከልከሉ ሲኣን/መድረክ ፊታቸውን ወደ ግል ኣዳራሾች በማዞር በሃዋሳ በሴንቴራል ሆቴል ኣዳራሽ የተከራዩ ቢሆንም፤ የሆቴሉ ባለቤት በገዥው ፓርቲ ኣባላት ማስፈራሪ እንደደረሳቸው በመግለጽ ለኣዳራሽ መከራያ የተሰጣቸውን ገንዝብ መልሰዋል።
 
የሆነ ሆኖ ለጉባኤው ሶስት ቀናት ሲቀሩት ሲኣን/መድረክ የጠራውን ህዝባዊ ጉባኤ ማካሄጃ ኣዳራሽ በገዥው ፓርቲ ተጽዕኖ ማጣቱን በመግለጽ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በመዘጋጀት ላይ እያለ ከሲዳማ ዞን ኣስተዳደር “እኛ እንደእናንተ ኣንሆንም” የምል መልዕክት ኣክሎበት የሲዳማ ባህል ኣዳራሽን እንዲጠቀሙ በስልክ መፈቀዱን ታውቋል።
 
ከዚህ ሁሉ ትግል በኃላ መሰብሰቢያ ኣዳራሽ ብገኝም በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ገዥው ፓርቲ ለክፍለ ከተማ እና ቀበሌ ካድሬዎች ኣበል በመክፈል የሲኣን ኣባላትን 1 5 ኣደረጃጀት በስራ እንደያዙ በማድረግ በጉባኤው ላይ እንዳይሳተፉ ኣድርገዋል።
ከዚህም ባሻገር ጉባኤውን በተመለከተ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ቅስቀሳ እንዳይካሄድ እና ስለ ጉባኤው የሚያትቱ በራሪ ወረቀቶች እንዳይስራጩ የከተማዋ ፖሊሶች ኣድርገዋል።
በተመሳሳይ በሲዳማ ዞን የወረዳ እና የቀበሌ ኮሚቴዎች የሲኣን ኣባላት በጉባኤው ላይ እንዳይሳተፉ በማስፈራራት እና 1 5 ኣደረጃጀትን በመጠቀም በስራ የማጥመድ ስራ ስርተዋል።
 
የሆነ ሆኖ የሲኣን/መድረክ ኣባላት እና ደጋፊዎች የገዥውን ፓርቲ ተጽዕኖ በመቋቋም በህዝባዊ ጉባኤው ላይ በመሳተፋቸው ጉባኤ በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ያለምንም ችግር በተሳካ መክሉ መካሄዱን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ዘግቧል።
 
 
 

No comments:

Post a Comment